የአዲስ አበባ መጽሀፍት አዟሪዎችና  በየትምህርት ቤቱ  ህፃናት  የሚጫኑት  ሸክም፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ወጣቶች መጽሀፍት እያዞሩ በመሸጥ ይተዳደራሩ፡፡ ሥራው የሚመሰገንና  የሚበረታታ ቢሆንም ለታዳጊ ወጣቶች ግን አደገኛ ነው፡፡

አንድ ታዳጊ ወጣት በአማካኝ በእጁ  እስከ 15 ኪሎ ግራም በጀርባው ደግሞ  እስከ 30 ኪሎ ግራም  መጽሀፍት ተሸክሞ  ከአንዱ የአዲስ አበባ ክፍል ወደ ሌላ አካባቢ  ገዥ ፍለጋ ሙሉ ቀን በእግር ሲኳትን  ይውላል፡፡

ይህ ከባድ ሸክም ለከፋ ጉዳት ያጋልጣቸዋል፡፡

  • በጊዜ ሂደት ለከፋ የጀርባ ህመም፣ የዲስክ መንሸራተት፣ የጡንቻና የነርብ ችግር ያጋልጣቸዋል፡፡
  • የማይመች ጫማ በማድረግ ከፍተኛ ግፊት  ጋር ረጅም ርቀት ስለሚጓዙ  ለእግር ችግር ያጋልጣቸዋል ፡፡
  • ታዳጊ አጥንታቸውን በማጉበጥ ቅርጻቸውን እነዲበላሽ  ያደርጋል ፡፡
  • የሚመገቡትና የሚያወጡት ሀይል ስለማይመጣጠን እድገታቸው ይገታል፡፡

solomon-at-work-ed                    spin

አንዳንዶቹ  ሽክፍ ያሉ በእጅ የሚገፉ ባለሁነት ጎማ አነስተኛ ተሸከርካሪ  ሲጠቀሙ መታየት የጀመሩ ነበሩ ሆኖም ደንብ  አስከባሪ  ስለሚከለክላቸውና ከተያዙም እሰከነ መጽሀፍቱ ስለሚዎርሷቸው ወደሸክማቸው ተመልሰዋል፡፡

solomon-stand                                 images-3

ስራው ህጋዊ ከሆነ ለምን በሸክም ብቻ እንዲሆን ተፈለገ ፡፡ በነተበና በተጎሳቆለ የጀርባ ሻንጣ በመጽሀፍ አጭቀው  ክንዳቸው ተወጥሮ  ጀርባቸው ተቀስፎ ራሳቸውን እየጎዱ ተመልካቹን ከሚያሳቅቁ ለማንም አደጋ የማይፈጥሩና የማያስቀይሙ ደረጃቸውን የጠበቁ ቁጥራቸው በሚታወቅ ትናንሽ ተሽከርካሪዎች ቢሠሩ ጉዳት ያለው አይመስለንም፡፡  መቸም ዱባይን ያየ ሠው የነዚህን ተሽከርካሪ ጥቅም የሚቃዎም ያለ አይመስለንም፡፡

መጽሀፍት አዟሪዎችን አልን እንጅ  የጉዳቱ  መጠን ባይነጻጸርም  በየትምህርት ቤቱ  ህፃናት የሚሸከሙት ኮተት ሀይ ባይ ያጣ ጉዳይ ነው፡፡

በተለይም የግል ትምህርት ቤቶች ያስጨበጡት እውቀት በሚሸከሙት ኮተት የሚለካ ይመስል  ለአንድ ትምህርት 3 ወይም 4 ደፍትር  የመንግስትና በግል ያሳተሟቸው መጽሀፍትና በልዩ ልዩ ስም በታተሙ የፎቶኮፒ ክምር ይጭኗቸዋል፡፡ የመምህራኑንና የልጆችን ዝርክርክነት ለመሸፈን ለቀኑ የሚያስፈልገውን በቻ እንዲወስዱ ድጋፍ አይደረግላቸውም፡፡ ለሁለም የትምህርት ዐይነት የሚያስፈልገውን ቁሣቁስ በየቀኑ እነዲሸከሙ ይፈረድባቸዋል፡፡

ስለእውነት ከሆነ ያ ሁሉ ኮተት አሰፈላጊ ሆኖ ሳይሆን ለትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ስለሚወሰድ ነው፡፡ ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ሌላ ልጅ እንዳይጠቀምበት ከላዩ ላይ እነዲጸፉበት ይደረጋል፡፡ በርከት ያሉ ልጆችን በግል ትምህርት ቤት የሚያስተምር ወላጅ  ከወጭው ባሻገር ማስቀመጫ የቸገረውን ቤቱ ይቁጠረው፡፡  ይህ ተግባር ለልጆች ጤና፣ ለቤተሰብ ጭንቀት፣ ለሚባክነው  የሀገር ንብረት፣ ለአካባቢ ብክለትና መራቆት ግድ ማጣት ነው፡፡

                 images-2                                       images-1

 

ተጨማሪ ማንበብ ከፈለጉ ዴይሊ ሜል ያወጣውን ዘገባ ይመልከቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like

No announcement available or all announcement expired.