አስር አደገኛ የደረጃ አጠቃቀም ልማዶች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ቢሮዎች፣ ትምህርት ቤቶች ወደ ህንጻዎች እየተቀየሩ፣ የግልም ሆነ የጋራ ሞኖሪያ ቤቶች ባለ በርካታ ወልል ህንጻዎች እየሆኑ ስለመጡ በሚሊዎን የሚቆጠር ህዝብ በቀን ደረጃዎችን ይጠቀማል፡፡ በዚህ በተለወጠና አዲስ አኗኗር ምክንያት በርካታ ወገኖቻችን ከደረጃ እየወደቁ የከፋ ጉዳት እየደረሠባቸው ይገኛል፡፡ ንጹሕ ኢትዮጵያ የሚሰተዋሉ ለአደጋ የሚያጋልጡ 10 የደረጃ አጠቃቀም ልማዶች/ስህተቶች ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል፡፡

 

1. የእጅ ስልክ እየነካኩ፣ መልእክት እተላላኩ ወይም እያነበቡ/እያዩ ከደረጃ መውጣትና መውረድ፡- ይህ የበርካታ ወጣቶችና በስራ ላይ ያሉ አዋቂ ሰዎች ችግር ነው፡፡

እግር የሚያርፍበት ቦታ በትክክ ላያስተውሉ መራመድ ሚዛንን አስቶ ለከፋ አደጋ ያጋልጣል፡፡ ወጣቶች፣ በከፍተኛ የሥራ ሃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች ይህን አደገኛ ሁኔታ አዘውትረው ሲፈጽሙ ይታያሉ፡፡

2. እጅን ከኪስ ከቶ ደረጃ መውረድ፡- ይህ የበርካታ ወንዶችና ወጣት ሴቶች ችግር ነው፡- እጅን ከሱሪ ወይም ከጃኬት ኪስ ከቶ ደረጃ መውጣትና መውረድ በከተሞች አካባቢ የተለመደ አጉል ልማድ ሲሁን ታስሮ እንደመራመድ ይቆጠራል፡፡ በሚወድቁበትም ጊዜ እጃቸውን ማስቀደም ስለማይችሉ ቀጥታ በፊታቸው፣ በጭንቅላታቸው፣ በመቀመጫቸው ስለሚሆን ጉዳቱ የከፋ የጀርባ አጥንት፣ የትክሻ፣ የአንገት፣ የጥርስና የጭንቅላት ስብራት የፊት መበላሸት ያጋጥማቸዋል፡-

3. ደረጃዎችንና መተላለፊያ ቦታዎችን በሚያጸዱበት ጊዜና በአጋጣሚ ርጥበት ስያገኛቸው የማስጠንቀቂያ ምልክት አለማድረግ ወይም ምልክት መኖሩን አለማስተዋል፡- አሁን አሁን የሚሰሩ ህንጻዎች መተላለፊያ ቦታዎችና ደረጃዎች በእምነበረድ ወይንም በለስላሣ ፖርስሊ የሚለብሱ በመሆናቸው እርጠበት ሲለካቸው በአደገኛ ሁኔታ የሚያንሸራትቱ ይሆናሉ::

   

4. ትንንሽና በግልጽ የማይታዮ ነጠላ ደረጃዎች ወይንም የወለሉ ከፍታ/ዝቅታ ለውጥ ሲኖር በምልክት ወይም በጽሁፍ ሰዎችን አለማሣወቅ፡- ወለሉ በነበረበት የሚቀጥል መስሏቸው በነጻነት በሚራመዱበት ወቅት ድንግት ሲቀየር የመውደቅ ወይንም ከፍተኛ የአካል መናጽ ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ በተለይ ሰዎች ከመጸዳጃ ቤት ሲወጡ፣ ከአንድ መተላለፊያ ወደሌላ ሲደርሱ ማስተዋልና ይኖርባቸዋል ከሁሉም በላይ ግን ህንጻውን የሚያስተዳደረው ለአብዛኛው ህዝብ በሚረዳው መልኩ ምልክት ማስቀመጥ አለበት፡፡

          

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may also like

No announcement available or all announcement expired.